የአሠሪና ሠራተኛ ዘርፍ ላይ የነበሩ ድክመቶች ለማረም የተለያዩ የሪፎርም ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛል፡፡
አቶ አሰግድ ጌታቸው
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ ዘርፍ የ6 ወር እቅድ አፈጻጸም እና የቀጣይ 6 ወር ዕቅድ ላይ ባለድርሻ አካት በተገኙበት ዉይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የአሠሪና ሠራተኛ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ አሰግድ ጌታቸው እንደገለጹት፤ በአዲሱ እሳቤ የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ የኢንዱስትሪ ሰላም ከማስፈን በላይ እንዲሁም የውጭ ስራ ስምሪት ጉዳይ ደግሞ የስራ እድል ፈጥሮ የውጭ ምንዛሬ ከማግኘት በላይ መሆኑን ግንዛቤ ተወስዶ የተለያዩ የሪፎርም ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛል፡፡
መድረኩ ባለፉት ወራት የነበሩ ማነቆዎችን በጋራ የሚገመገሙበትና በቀጣይ በትኩረት ስለሚሰሩ ስራዎች መግባባት የሚፈጠርበት ይሆናል ብለዋል፡፡
በውጭ ሀገር ስራ ስምሪት ዙሪያ የስራ አካባቢን ምቹ ከማድረግ ጀምሮ ፋይሎች በዘመናዊ መልክ የማደራጀት እንዲሁም የሥራ ፍሰትን ተከትሎ እንዲሄድ በዘመናዊ ሲስተም የሚመራ ቀልጣፋና ጊዜ ቆጣቢ የሆነ አሰራር መተግበር መጀመሩ ተጠቁሟል።
ታህሳስ 20/2015፤ ሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
ለወቅታዊን ትኩስ የሥራና ክህሎት መረጃዎች
ቴሌግራም፦https://t.me/fdre_mols በመወዳጀት ይከታተሉን::
No comments:
Post a Comment